ለግምገማው(ዎቹ) የጊዜ-ሰሌዳ መያዝ እንዲሁም ምሳሌ አንቀጦች
ለግምገማው(ዎቹ) የጊዜ-ሰሌዳ መያዝ. ተገቢ-የሆነውን የአገልግሎት-ሰጪ ከመረጣችሁ በኋላ፤ ለተማሪያችሁ የሚያስፈልገውን ግምገማ(ዎች) ለማድረግ - ቀን(ናቶች)ን የጊዜ-ሰሌዳ ያዙ። የጊዜ- ሰሌዳውን በምትይዙ ጊዜ፣ የሚከተሉት ላይ እርግጠኛ ሁኑ: • የየግል የትምህርት ግምገማ (independent educational evaluation (IEE)ን ለማድረግ፣ ከDCPS ፈቃድ-መስጫን እንዳገኛችሁ ግለጹ። አገልግሎት-ሰጪዎች - የየግል የትምህርት ግምገማዎች (independent educational evaluations)ን በመደበኛነት ሊያካሂዱ የሚችሉት፤ ፈቃድ-መስጫ ቅጹን እና ክፍያውን ወደ DCPS/OSSE በቀጥታ-ማስከፈል መቻላቸውን የሚያሳየው ቅጽ ሲሰጣቸው ነው። • አገልግሎት-ሰጪው የሚያካሂደው - ትክክለኛ የሆነውን ግምገማ መሆኑን አረጋግጡ። • ግምገማው የት እንደሚካሄድ፣ አረጋግጡ። • ግምገማው የጊዜ-ሰሌዳ ሲያዝለት፤ ለተማሪያችሁ ትምህርት ቤት አሳውቁ። ይህን ማድረጋችሁ፤ DCPS የተጠናቀቀውን ግምገማ ለመቀበል እንዲጠባበቅ ያደርገዋል።