Contract
አዋጅ ቁጥር 2015
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት መካከል የተደረገውን በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የሕግ ትብብር ስምምነት ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት መካከል በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የሕግ ትብብር ስምምነት እ.ኤ.አ. መስከረም 21
ቀን 2022 በአቡዳቢ የተፈረመ በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
1. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ “በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት መካከል የተደረገውን በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የሕግ ትብብር ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር..../2015” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2. ስምምነቱ ስለመጽደቁ
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት መካከል እ.ኤ.አ. መስከረም 21 ቀን 2022 በአቡዳቢ የተፈረመው በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የሕግ ትብብር ስምምነት ፀድቋል፡፡
3. የኢ.ፌ.ዲሪ የፍትሕ ሚኒስቴር ኃላፊነት
የኢፌዴሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ይህን ስምምነት ለማስፈጸም አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ሁሉ እንዲወስድ በዚህ አዋጅ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡
4. አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል:: አዲስ አበባ.......... ቀን….. 2015 ዓ.ም.
ሳህለወርቅ ዘዉዴ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት